Welcome
Login / Register

ቅስና የሌለው ሰው አያጠምቅም አያናዝዝም ፣ አይባርክም /ፍት/ ነ.ፍ.መ አን 3 .ቁ. 21 / ……..ሀብተ መንፈስ ቅዱስ በገንዘብ አይሸጥምና አጥማቂው ካህን መማለጃ መቀበል አይገባውም ። / ፍ .ነ .ፍ መ አን 7 /

በእጃቸው ትልቅ የእንጨት መቁጠሪያ እና ትንሺዬ መስቀል በመያዝ በየአብያተ ክርስቲያኑ ምእመናኑን ፀበል በመርጨትና አጋንንትን ” በማስወጣት ” ይታወቃሉ ፣ የእርሳቸው መቁጠሪያ አርፎበት እየጮኸ ያልወጣ አጋንንት የለም ነው የሚባለው ። እርሳቸውም  በመቁጠሪያ የሰውዬውን ጀርባ እየቀጠቀጡ አጋንንትን እንዴት ማውጣት እንደሚቻል በ2005 ዓም ” በማለዳ መያዝ የክፉ መንፈሶች ድርጊት ” በሚል ርእስ ባሳተሙት መፅሀፍ ላይ በገፅ 155

 

/ በቤተክርስቲያኛችን ካህናትና በንስሀ አባቶቻችን በተባረከ መቁጠሪያ በእግዚአብሄር አምላክ ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ፣ በእመቤታችን ድንግል ማርያምና በቅዱሳን መላእክት ስም ሁለቱ ትከሻዎቻችን መሀል ስንቀጠቀጥ ወይም ስንመታ የማቃጠል የመለብለብና የመውረር ወይም የመንዘር የመብላት ወይም የማሳከክ ከአንዱ የሰውነት ክፍላችን ወደሌላው የመዞርና እንደ ድንጋይ በድን መሆን ፣ እንዲሁም ጭንቅላታችንን ለሁለት ከፍሎ ፣ የራስምታት አይነት ስሜት ከተሰማን ሰይጣን ውስጣችን አለ ማለት ነው)  በማለት የመቁጠሪyaን ሀያልነትና ሰይጣን በውስጡ ያለ ሰው የሚታሳየውን Meላሽ በመፅሀፋቸው ፅፈዋል ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቀኖና የመምህር ግርማ አገልግሎትን በተመለከተ ምን ይላል ?
……ቅስና የሌለው ሰው አያጠምቅም አያናዝዝም ፣ አይባርክም /ፍት ነፍመአን 3 ቁ 21 /
……ቅዱሱን ቅባት መቀባት የሚችለው የክህነት ስልጣን ያለው ብቻ ነው ። ያዕ 5;14 /
……ሀብተ መንፈስ ቅዱስ በገንዘብ አይሸጥምና አጥማቂው ካህን መማለጃ መቀበል አይገባውም ። / ፍ .ነ .ፍ መ አን 7 /

መምህር ግርማ አገልግሎታቸውን በስፋት በጀመሩበት የደብረሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን የሰንበት ት/ቤት ከአመታት በፊት የተነሳው ውግዘት መፍትሄ አግኝቶ የአዲስ አበባ ፓሊስ ዛሬ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል ።
ከላይ በቤተክርስቲያኒቱ ህገ ደንብ በተጨማሪ መምህር ግርማ በአዲስ አበባ ካሉ አንዳንድ የሰንበት ትምርት ቤቶች ena በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት የሚገኙ 12 የሰንበት ት/ ቤቶች በጋራ በመሆን ባቀረቡት የውግዘትና የቅሬታ ደብዳቤ ላይ እንዳመለከቱት መምህሩ የሚያካሂዱት የማጥመቅ ስራ የቤተክርስቲያኒቱን ህግ ይጣረሳል በድቁና የሚያገለግል ሰው ይላላካል እንጂ አያጠምቅም የሚለው አንዱን ቅሬታ በማስመልከት መምህሩ ሲመልሱ በርግጥ ከዚህ በፊት ቤተክህነት ፊት ቀርቤ የቅስና ማእረግ የለኝም ያልኩት  በስህተት ነው እንጂ እኔ ቄስ ነኝ ስለዚህም ማጥመቅ እችላለሁ ብለው ከኢትዮጵያ ቤተክህነት እውቅና ውጭ  በኢትዮጵያ በአውሮፓና አሜሪካ ለተወሰኑ አመታት በማጥመቅ ሲያገለግሉ ቆይተዋል ።
አንዳንድ ምእመናን ስለመምህር ግርማ ሲናገሩ ከቤተ ክርስቲያን እውቅና ውጭ ፣ ቪሲዲ ፣ ጋዜጣ ፣ መፅሄትና ለፈውስ ይረዳል ያሉትን ዘይት በተደራጀ አኳሁዋን ለገበያ በማቅረብ የዘመናዊ መኪና ባለቤት ከመሆናቸው በተጨማሪ ከቤተ ክርስቲያን ውጭ በ አንድ ሚሊየን አምስት መቶ ሺህ ብር በገዙት ዘመናዊ መኖሪያ ቤታቸው የፀበል ማጥመቅና የፈውስ አገልግሎት መስጠታቸውም ሌላው ከምእመናን ጋር የሚጋጩበት ጉዳይ ነው ።

Source; KonjoEthiopia

Related Articles

Post your comment

Comments

Be the first to comment