Welcome
Login / Register

በአለማችን ይኖራሉ ብለው የማይገምቷቸው አስገራሚ ድረ ገፆች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሁኑ ወቅት መጠኑ ይለያይ እንጂ አንዳንዶቻችን በየቀኑ የኢንተርኔት መረቦችን መቃኘታችን የተለመደ ተግባር ሆኗል።

የምንቃኛቸው ድረ ገፆችም ብዙ ጊዜ የምናውቃቸውን አልያም በጣም ታዋቂዎቹን ነው።

አንዳንድ ጊዜም በፌስቡክ አማካኝነት ያገኘናቸው መረጃዎች አዳዲስ ድረ ገፆችን ያስተዋውቁናል።

እነዚህን አዳዲስ ድረ ገፆችም ጠቃሚ ሆነው ስናገኛቸው ለሌላ ጊዜ እንድንጠቀማቸው ቡክማርክ አድረገን እናስቀምጣቸዋለን።

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት 9 ድረ ገፆች ግን ምናልባትም አይተናቸው የማናውቃቸው እና የተለየ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው ይላል ቴክወርም የተሰኘው የቴክኖሎጂ ድረ ገፅ ዘገባ።

 

1. 10Minutemail.com

ይህ ድረ ገፅ ለ10 ደቂቃ የሚቆይ የኢሜል አድራሻ ለመክፈት ያስችላል።

ድረ ገፁ የተላላክናቸውን መልዕክቶች እና የኢሜል አድራሻውን ከ10 ደቂቃዎች በኋላ ሙሉ በሙሉ ያጠፋዋል።

10Minutemail.com እንደከፈትነው ምንም ምዝገባ ሳያስፈልገን ራሱ የኢሜል አድራሻ ይሰጠናል።

2. የሀሰት ስም እና አድራሻ ፈጣሪ - Fake Name Generator

በጣም አይነአፋር የሆኑ፣ የግል ጉዳያቸው የሚያስጨንቃቸው እና ትክክለኛ ስማቸውን ይፋ ማድረግ የማይፈልጉ ሰዎች በዚህ ድረ ገፅ አማካኝነት የሀሰት ስም እና ዝርዝር መረጃዎችን መፍጠር ይችላሉ።

Fakenamegenerator.com  

3. አንዳንድ ድረ ገፆች የማይከፍቱት እንዳልከፍታቸው ስለታገድኩ ነው ወይስ ስለማይሰሩ? - Down for Everyone or Just Me

አንዳንድ ጊዜ ኮምፒውተርዎ የተወሰኑ ድረ ገፆችን አልከፍት ሊልዎት ይችላል። እናም በዚህ ድረ ገፅ አማካኝነት እውን ይህ ድረ ገፅ አልከፍት ያለዎት ስለማይሰራ ነው አልያስ ሆን ተብሎ እንዳይከፍቱት ስለተደረገ ነው የሚለውን ማረጋገጥ ይችላሉ።

Downforeveryoneorjustme.com 

4. የቀናት ልዩነትን ለማስላት - Date and Time 

በዚህ ድረ ገፅ ደግሞ በቀናት እና አመታት መካከል ያሉ ልዩነቶችን ለማስላት ይጠቅማል።

ለአብነትም እድሜያችን በቀናት ለማስላት የተወለድንበትን ቀን፣ ወር እና አመት እና የእለቱን ቀን ወር እና አመት በማስገባት በምድር ላይ ለስንት ቀናት ቆይታ እንዳደረግን ማስላት እንችላለን።

የምናሰላው ቀን በአላትን እና ቅዳሜ እና እሁድን አካቶ አልያም ሳያካትት ስንት እንደሆነም ማወቅ ያስችላል።

timeanddate.com 

5. የድረ ገፆችን የፊት ገፅ ምስል ለማስቀረት - Web Capture

የተለያዩ ድረ ገፆችን የፊት ገፅታ ምስል ለማስቀረት እና ወደ JPG/JPEG፣ PNG አልያም PDF ፎርማት ለመቀየር ይህን ድረ ገፅ ይጠቀሙ። 

webcapture.net/  

6. ጎግልን ያለምንም የሀገር ገደብ ለመጠቀም - Google NCR

የጎግል ድረ ገፅን (google.com) ስንከፍት ጎግል ወደየሀገራችን ዶሜን ያስገባናል። ለምሳሌ ጎግልን በኢትዮጵያ ስንከፍት google.com.et ወደሚለው ያሸጋግረናል። ይህም የሚሆነው ጎግል እንደየሀገራቱ የሚከለክለው እና የሚፈቅደው ስላለው ነው።

እናም ጎግልን ያለምንም የሀገራት ገደብ ለመክፈት google.com/ncr ብለን መፈለግ በቂ ነው።

7. የተላኩልን ፋይሎች በቫይረስ የተጠቁ መሆን አለመሆናቸውን ለማረጋገጥ - Virustotal

ከጓደኞቻችን አልያም ከማናውቀው ግለሰብ የሚያጠራጥር ፋይል ከተላከልን እና ከኢንተርነየት በቀጥታ ካወረድነው በዚህ ድረ ገፅ አማካኝነት የተላከልን ፋይል ቫይረስ መያዙን እና አለመያዙን ማወቅ እንችላለን።

ቪሩስቶታል ነፃ የኢንተርኔት የቫይረስ መመርመሪያ (ስካነር) ነው።

8. በአለማችን እየተከናወኑ ያሉ ወቅታዊ የመረጃ ዘረፋዎችን የሚያሳይ ካርታ - IPviking

በአለም ዙሪያ እየተከናወኑ ያሉ የመረጃ ምንተፋዎች፣ የአይፒ አድራሻዎች፣ የመረጃ ዘራፊዎቹን አድራሻ እና የመሳሰሉ መረጃዎችን http://map.norsecorp.com/#/ በተባለው ድረ ገፅ ላይ መመልከት ይቻላል።

9. Hackertyper

ይህን ድረ ገፅ ከፍተን የተለያዩ ፊደላትን እና ቁጥሮችን ስንጫን መረጃ ዘራፊዎች የሚጠቀሙበትን አይነት ገፅ ይከፍትልናል።

በዚህም ጓደኞቻችን እና ወዳጆቻችን የተለያዩ ድርጅቶችን መረጃዎችን እየሰረቅን ለማስመሰልና ለመሸወድ እንችላለን።

http://hackertyper.net/

 

ምንጭ፦ www.techworm.net/

Related Articles

Post your comment

Comments

Be the first to comment