Welcome
Login / Register

አይናችንን የሚጎዱ እና ለመከላከል ማድረግ ያለብን ተግባራት

በእለት ተእለት ተግባራችን ውስጥ የተለያዩ ስራዎችን ስንከውን እንውላለን። ነገር ግን በብዛት የምንሰራቸው ስራዎች ላይ ጥነቃቄ ካልታከለበት በጤናችን ላይ ጉዳት እንደሚያደርስ ይታወቃል። በእለት ተእለት ተግባራችን ውስጥ ለአደጋ ከሚጋለጡት እና ከፍተኛ ጥንቃቄን ከሚሹ የሰውነት ክፍላችን ውስጥ አንዱ አይናችን ነው።

በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ የአይን ህክምና ባለሙያ የሆኑት ዶክተር ኪምበርሊይ ኮኬርሃም፥ አሁን አሁን በርካታ ወጣቶች ላይ የአይን ጤና ችግር በብዛት እየተስተዋለ መጥቷል ይላሉ። ይህ ሊሆን የቻለውም በእለት ተእለት እንቅሰቃሴያችን ውስጥ የተለያዩ ስራዎችን ስንሰራ ለአይናችን ተገቢውን ጥንቃቄ ስለማናደርግለት ነው ሲሉም ይናገራሉ።

አሁን ላይ በብዛት ለአይን ህመም መንስዔ እየሆኑ ከሚገኙ ነገሮች ውስጥ የስክሪን አጠቃቀማችን ማለትን እንደ ላፕቶፕ፣ ስማርት ስልክ፣ ቴሌቭዥን እና ታብሌት ስክሪን በዋናነት ይጠቀሳል።

ከዚህ በተጨማሪም ከፍተኛ የሆነ ጭንቀት፣ ጤናማ ያልሆነ የአመጋገብ ስርዓት፣ ሲጋራ ማጨስ እና ከመጠን ያለፈ የሰውነት ክብደትም ለአይን ህመም መንስኤ መሆናቸውን ዶክተር ኪምበርሊይ ይናገራሉ።

አይናችንን የሚጎዱ እና ለመከላከል ማድረግ ያለብን ተግባራት…

  1. የስክሪን አጠቃቀማችን

ከኤሌክትሮኒክስ ቁሶች ስክሪን የሚወጣው ሰማያዊ ብርሃን የአይናችን እይታ ላይ ጉዳት ከሚያደርሱት ውስጥ አንዱ ነው። ከዚህ በተጨማሪም ረጅም ሰዓት እንደ እንደ ላፕቶፕ፣ ስማርት ስልክ፣ ቴሌቪዥን እና ታብሌት ስክሪኖች ላይ በምናሳልፍበት ጊዜ አይናችን በመሃል እየጨፈንን እረፍት የማንሰጠው ከሆነ ለአይን መድረቅ፣ ለአይን ህመም እና የአይናችን እይታ እንዲደክም ያደርጋል።

vision-eyesight-eyes-sore-tired-strain-screensየስክሪን አጠቃቀማችን

በስክሪን ምክንያት እንዲህ አይነት ችግሮች እንይከሰትብን በአይናችን እና በስክሪን መካከል ያለው ርቀት ቢያንስ 16 ኢንች መሆን አለበት የተባለ ሲሆን፥ ከዚህ በተጨማሪም በስክሪኑ ላይ የምናየውን የፅሁፍ መጠን ማሳደግ ለአይናችን ጤንነት ይረዳል።

READ  ጤናማ እንቅልፍን ለመተኛት የእንቅልፍ ሳይንቲስቱ ሶስት ነገሮችን ይመክራሉ

2. ጭንቀት

ሰዎች በሚጨነቁበት ጊዜ የሚያመነጩት ኮርቲሶል የተባለ ሆርሞን በአይን ላይ እክል ይፈጥራል ተብሏል።በጭንቀት ወቅት የሚመነጨው ሆርሞንም እይታችን እንዲደበዝዝ ማድረግ እንደሚችልም ነው ባለሙያዎች የሚናገሩት። በጭንቀት አማካኝነት የሚከሰተውን የእይታ እክል ለመከላከልም ጭንቀትን የሚያስወግዱ እንደ አካል ብቃት እንቅስቃሴ ያሉ ተግባራትን መከወን መልካም ነው፤ በዚህም የኮርቲሶል መጠንን በ25 በመቶ በመቀነስ በአይናችን ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት መቀነስ ይቻላል።

3. የምናነበውን ነገር ለአይናችን በጣም ማቅረብ

ከመፅሃፍትም ይሁን ከስልካችን ላይ የምናነባቸውን ነገሮች ወደ አይናችን በጣም የምናቀርብ ከሆነ ይህም በይናችን ጤንነት ላይ እክል ይፈጥራል የሚለውም ተቀምጧል። በዚህ መልኩ የሚከሰት የአይን ጤና እክልን ለመከላከልም በምናነብበት ጊዜ 20-20-20 ህግን መተግበር መልካም ነው።ይህም በምናነብበት ጊዜ በ20 ደቂቃ ልዩነት ለአይናችን እረፍት መስጠት ሲሆን፥ በዚህ ጊዜም ራቅ ወዳሉ እና ለየት ያሉ ነገሮችን መመልከት መልካም ነው።

4. ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ በአይን ላይ የሚያመጣው እከል

በአመጋገባችን ውስጥ አትክልት እና ፍራፍሬን የማናካትት ከሆነ ለአይናችን ጠቃመኒ የሆኑ እንደ ኒትሬትስ እና ሉተዪን ያሉ ንጥረ ነገሮችን እንዳናገኝ ያደርጋል። በዚህ መልኩ በአይናችን ላይ የሚደርሱ የጤና እክሎችን ለመከላከልም አትልክቶችን አዘውትሮ መመገብ መልካም ነው፤ በእለት ምግባቸው ውስጥ 240 ሚሊግራም አትክልት አካተው የሚመገቡ ሰዎች ለግላኮማ የመጋለጥ እድላቸውን በ30 በመቶ እንዲቀንሱ ያስችላቸዋል።

www.menshealth.com

Related Articles

  • የሚግሬን ራስ ህመም ምን...

    የሚግሬን ራስ ህመም ምንድን ነው (What is a Migraine headache)(በዳንኤል አማረ ©ኢትዮጤና) ሚግሬን የራስ ህመም በአእምሮ ...

  • አያት የልጅ ልጃቸውን ወለዱ

    አያት የልጅ ልጃቸውን ወለዱ አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሜሪካ ሰሜናዊ ቴክሳስ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ...

  • ስለ ደም ዓይነቶች ምን ...

    (በዳንኤል አማረ ©ኢትዮጤና) የደም ዓይነት በቀይ የደም ሴሎች ሽፋን(ገጽ) ላይ የሚገኝ በውርስ የወሰድነውን አን...

Post your comment

Comments

Be the first to comment