Welcome
Login / Register

የኢህአዴግ አንድ ሀሙስ ቀረው ጨዋታ…..

የኢህአዴግ አንድ ሀሙስ ቀረው ጨዋታ….. | ማዕረግ ጌታቸው በድሬቲዩብ

የኢህአዴግ አንድ ሀሙስ ቀርቶታል ጨዋታ ድፍን 27 አመት ሊሞለው እየተንደረደር ይገኛል ፡፡በዚህ ጊዜ ውስጥ ኢህአዴግ እንደ እባብ ስንቴ አፍረ ልሶ ዳግም ነፍስ ዘራ ? ስንቴስ የድመት ነፈስ ያለው መሆኑን አሳየ ? አዕላፍ ጊዜ ፡፡ልደቱ አያሌው “መድሎት “በተሰኘ መጽሐፉ የኢትዮጵያ የተቃውሞ ጎራ አንዱ መሰራታዊ ችግሩ ሁሌም ኢህአዴግ አብቅቶለታል እያለ ማሰቡ ነው ይላል ፡፡እንዲ ብሎ በማሰቡም የረጅም ጊዜ ዕቅድ አውጥቶ ኢህአዴግን ለማውረድ ከመታገል ይልቅ ኮሽ ሲል ከያሉበት ተሰባስቦ ሰልፍ በመጥራትና የሞች ቁትር ተጭበርብሯል በሚል ንትርክ ላይ እንዲጠመድ አደረገው ፡፡

ይህ አይነቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ መንግድ በንትርክ ብቻ የሚቋጭ ሳይሆን በየጊዜው የሚነሱ የህዝብ ተቃውሞዎችን መናሻ በማድረግ ኢህአዴግ አበቃለት በሚል የጉሮ ወሸባየ የድል ዜማ የታጀበ ነው ፡፡በኢህአዴግና ኢህአዴጋዊ ባልሆነ ምክንያት እንደ ዛሬው የተቃዋሚ ጎራ ተዳክሞ እንጠፍጣፊው ሳይቀር ፤ በ1980ዎቹ አዕላፍ ተከታይ የነበራቸው ቡድኖችና ግለሰቦች ኢህአዴግ አንድ ሀሙስ ቀርቶታል አይዞህ ጎበዝ እያሉ ህዝቡን ሲያታግሉ ኑረዋል ፡፡ግን ለኢሀዴግ ጀሌ ሁነው የይስሙላ ዲሞክራሲ ማዳመቂያ ከመሆን ውጭ የፈየዱት ነገር አንዳችም አለነበረም ፡፡

በ1990ዎቹ የነበረሩት ተቃዋሚዎች ኢህአዴግ አብቅቶለታል የጸጥታ ዘርፉ ሳይቀር ክዶታል እያሉን ያችኑ አንድ ሀሙስ ሲያስጠብቁን ኑረዋል ፡፡ባለፉት ሁለት አመታትም ደሃው ኢትዮጵያዊ ጎዳና ሲወጣ ይኼው ዜማ ከፍ ብሎ መሰማቱን ቀጥሏል ፡፡የድሃ ልጅ የሚከፈለውን የሕይወት መሰዋትነት ፖለቲከኞቻችን አሁንም የድል ነጋሪት እያደረጉት መጓዝን መርጠዋል ፡፡እዚህ ላይ ከትናንቱ የተለየ ምን ነገር ስላለ ተቃዋሚውን ጎራ አምነን ኢህአዴግ አንድ ሀሙስ ቀረው እንበል የሚል ጥያቄ ማንሳቱ ነውርነት የለውም ፡፡

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ህዝብን ቤተ-ሙከራው ያደረገ አሰነዋሪ ጨዋታ ነው ፡፡ኢህአዴግ ስልጣኑን የሚቀናቀኑት ሃይሎችን በህዝብ ለማስጠላት በህዝብ ደም እሰከመቆመር የደረሰ ድርጊት ውስጥ እንደተዘፈቀ የአደባባይ ሚሰጥር ሁኖ ዘልቋ፡፡ ይህ አይነቱ ባህሪ ግን ለኢህአዴግ ብቻ የተጠው አድርጎ ማሰቡ ቂልነት ነው ፡፡ግማሽ መዕተ አመት የተሸገረው የኢትዮጵያ የፓርቲ ፖለቲካ በመጠላላት ላይ ያተኮረና ህዘብ ለስልጣን መቆናጠጫ ኮርቻ ከማድረግ ያልዘለለ ነው ፡፡

ለእንዲህ አይነቱ የሀገራችን ፖለቲካ መቆርቆዝ ሁለት ምክኝቶችን በቀላሉ መጥቀስ ይቻላል ፡፡የመጀመሪያው ፖለቲካችን ከግራ ፖለቲካ አራማጆች አለመላቀቁ ነው ፡፡ኢህአዴግም ሆነ አብዛኛው የተቃውሞው ጎራ አራማጆች በግራ ፖለቲካ የተጠመቁ አብዮተኞች በመሆናቸው እንደ ኤንግልስ የእንቁላሉን አስኳል ለማግኘት የግድ እንቁላሉ መሰበር አለበት የሚል አሰተሳሰብ አላቸው ፡፡ይህ ደግሞ የትናንቷን ብቻ ሳይሆን የነጋዋም ኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ተስፋ የሌላት ሀገር ያደርጋታል ፡፡

ሁለተኛው ምክንያት የተቃውሞው ጎራ ፖለቲከኞች የተደራጀ የፖለቲካ አጀንዳ የሌላቸው መሆኑ ነው ፡፡በእኔ ምልከታ ከኢዴፓ ፓርቲ ውጭ (የቅንጅት ፓርቲ ማኒፌስቶ ከኢዴፓ ሙሉ በሙሉ የተወሰደ ስለሆነ ነው )የራሱ የሆነ ጠንካራ የፖለቲካ ፕሮገራም ይዞ የዘለቀ ፓርቲ በሀገራችን ማግኘት አዳጋች ነው ፡፡ይህ በመሆኑም ተቃዋሚ ፓርቲዎች በሀገሪቱ ህዝበዊ ተቃውሞ ሲነሳ አልያም የምርጫ ሰሞን የምትለቀቅን ፍርፋሪ ለመሻማት ተሯሩጠው መግለጫ ይሰጣሉ ፡፡

የህዝብን ደም ቤተ-ሙከራ የሚያደረገው የኢትዮጵያ ፖለቲካ በአንዱ ካልተሳካ በሌላው ይሳካል እያለ ዛሬም አዕላፍ የኔን ዘመን ሰዎች ያስጨርሳል ፡፡ህዘቡን በበሳል የፖለቲካ ፕሮግራም መርቶ ከሚፈለገው ደረጃ ለማድረስ ከመጣር ይልቅ ኮሽ ሲል አቧራ የተጫነውን ማህተም ከመሳቢያ መዞ ወረቀት ላይ በማሳረፍ የኢህአዴግን አንድ ሀሙስ ቀረው ላማወጅ ይሯሯጣል ፡፡

በእኔ ዕምነት የኢህአዴግ አንድ ሀሙስ ቀረው ጨዋታ ከኢሀዴግ በላይ የጠቀመው አካል የለም ፡፡አንድ ሀሙስ ቀርው እየተባልን አዕላፍ ዘመናትን መሻገራችን በሀገራችን ፖለቲካ ተስፋ እንድንቆርጥ አደረገን ፡፡አቶ ልደቱ እንደሚለውም ኢህአዴግን መቼም የማይወርድ ፓርቲ አድረገን እንድናሰበው አሰገደደን ፡፡በዚህ የፖለቲካ አሰተሳሰብ መነሾ ኢህአዴግ ስንቴ ሙቶ ስንቴ ሲነሳ እንደማይናከስ ውሻ ጩኸት የሚያበዙት የሀገራችን ፖለቲካ ፓርቲዎች ባሉበት ሲዳክሩ ከዛሬ ደጃፍ ደረሱ ፡፡

የኢህአዴግ አንድ ሀሙስ ቀረው ጨዋታ ከኢህአዴግ ባላይ ማንን ጠቀመ ? ማንንም ፡፡ተቃዋሚው ጎራ በድል ጮቤ እየረገጠ አዕላፍ አመታትን ቢሻገርም አሁንም ቤተ-መንግስት መግባት አይደለም በዛ ማለፍ አልቻለም ፡፡ከአንድ ሀሙስ ፖለቲካዊ ጨዋታ ሳንላቀቅ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የትም ልናደረሰው አንችልም ፡፡
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከአለም ነባራዊ ሁኔታ ውጭ አይደለም ፡፡ይህ በመሆኑም የተጠና የፖለቲካ አካሄድ ሳይኖር የሚደርግ የፖለቲካ ትግል ውጤቱ በዜሮ የተባዛ ነው ፡፡ለዚህ ዋናው ተጠያቂ የአንድ ሀሙስ ቀረው ፖለቲካዊ ጨዋታ ሱስ ስለሆነብን ነው ፡፡ DireTube

Related Articles

Post your comment

Comments

Be the first to comment