Welcome
Login / Register

የኢትዮጵያ ወዳጅ ፕሮፈሰር ሪቻርድ ፓንክረስት በ90 ዓመታቸው አረፉ / Historian Professor Richard Pankhurst Passed Away at 90.

የኢትዮጵያ ወዳጅ ፕሮፈሰር ሪቻርድ ፓንክረስት በ90 ዓመታቸው አረፉ / Historian Professor Richard Pankhurst Passed Away at 90.

 የታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር ሪቻርድ ኬር ፔቲክ ፓንክረስት 

• በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ባደረጉት ጥልቅ ጥናትና ምርምር ከአፄ ኃይለሥላሴ ሽልማት ድርጅትና ከእንግሊዝ መንግሥት የወርቅ ሚዳሊያና ኒሻን ለመሸለምም በቅተዋል።

• ለኢትዮጵያ በመወገን እንደ አርበኛዋ እናታቸው ፀረ- ፋሽስት ጽሑፎችን በጋዜጣ በማውጣት ትግል የጀመሩት ገና የዩኒቨርሲቲ ተማሪ እያሉ ነበር።

• ከሃያ በላይ መጻሕፍት ጽፈዋል። የተወሰኑት መጽሐፍት ለአገራችን ዩኒቨርሲቲዎች የመማሪያና የምርምር ሰነዶች ለመሆን በቅተዋል።

• ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከሃምሳ ዓመት በላይ ሠርተዋል። ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ለደረሰበት የዕድገት ምዕራፍ የታሪክ ባለድርሻ አድርጓቸዋል።

• አገራችንን ለዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ ያስተዋወቁ፣ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩትን በመመስረት እንደእናታቸው የዘመን ተሻጋሪ ታሪክ ባለቤት ለመሆን ችለዋል።

• የአክሱም ሐውልትን፣ የአፄ ቴዎድሮስ ክታብንና ሌሎችንም ቅርሶችን እንዲመለሱ በማድረግ ሕዝባችን ለዘመናት ከነበረበት ፀፀትና ቁጭት እንዲላቀቅ አድርገዋል።

• የአገር ባለውለታ ምሁር የሃምሳ ዓመት ወርቃማ አገልግሎት ለመዘከር በተዘጋጀ ልዩ ሥነ ሥርዓት ላይ በብር የተሰራ የአክሱም ሐውልት ምስል ተሸላሚ ሆነዋል።

• የተወለዱት እ.አ.አ በወርሃ ታህሣሥ 1927 በአገረ እንግሊዝ ለንደን ከተማ በሚገኘው ሐምስቴድ ሆስፒታል ነው።

• የለንደን ዩኒቨርስቲ ተማሪና የዛሬው እውቅ የታሪክ ምሁር የሦስት ዓመት የዩኒቨርሲቲ ቆይታቸውን አጠናቀው በሃያ አንድ ዓመታቸው በምጣኔ ሀብት (Economics) የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በማዕረግ አግኝተዋል።

• በሃያ ዘጠኝ ዓመታቸው በምጣኔ ሀብት ታሪክ (Economic History) የዶክተሬት (PHD) ዲግሪያቸውን እ.አ.አ በ1954 በከፍተኛ ውጤት ተመረቀዋል።

• በአምስት ዓመቱ የጣሊያን ወረራ ወቅት ከኢትዮጵያ ጎን የነበሩት የሲልቪያ ፓንክረስት ወንድ ልጅ የሆኑት ፕሮፌሰር ፓንክረስት ወደ ኢትዮጵያ የመጡት እ.አ.አ በ1956 ነበር፡፡

• ለአገራችን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማሪያና እና ለዓለም አቀፍ ተመራማሪዎች ደግሞ ማጣቀሻ የሚሆኑ ከሃያ ሁለት በላይ መጽሐፍትን ለሕትመት አብቅተው ለትውልድ ሁሉ የሚተላለፉ ሕያው ቅርስ አበርክተዋል።

• ከ400 በላይ የተለያዩ የምርምር ጽሑፎችን በመፃፍ ለዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ ለንባብ አብቅተዋል።

• እ.አ.አ ከ1956 ዓ.ም ጀምረው በመምህርነት፣ በጥናት ምርምር ውጤታቸውና ክህሎታቸው በፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያበቃቸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መጠነ ሰፊ ለሆነው ምሁራዊ አስተዋፅኦአቸው የክብር ዶክትሬት (PHD) ዲግሪ አበርክቶላቸዋል።

• ለባለቤታቸው ሪታ ፓንክረስት፣ ለልጆቻቸው ለሄለን ፓንክረስት እና አሉላ ፓንክረስት እንዲሁም ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንመኛለን።

ነፍስ ይማር!

Related Articles

  • መንግሥት የወልቃይት ጠ...

    የጎንደር ሠልፍ ተገቢ ጥያቄዎችን እንደያዘ ክልሉ አሳወቀ በባህር ዳር ከተማ የተካሄደውን ሁለተኛውን አገር አቀ...

  • ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ ዶ/ር ...

    ፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለማስወገድ ሙከራ አድርገዋል በሚ...

  • EPRDF Sleeping While Innocent People ar...

    Aigaforum) Nov 06, 2017 - Ethiopia is passing through tough times! Innocent people from north to south, west to east are being killed in broad day light! This has been going on for a...

Post your comment

Comments

Be the first to comment