Welcome
Login / Register

Health Link ጤና


 • አይናችንን የሚጎዱ እና ለመከላከል ማድረግ ያለብን ተግባራት

  በእለት ተእለት ተግባራችን ውስጥ የተለያዩ ስራዎችን ስንከውን እንውላለን። ነገር ግን በብዛት የምንሰራቸው ስራዎች ላይ ጥነቃቄ ካልታከለበት በጤናችን ላይ ጉዳት እንደሚያደርስ ይታወቃል። በእለት ተእለት ተግባራችን ውስጥ ለአደጋ ከሚጋለጡት እና ከፍተኛ ጥንቃቄን ከሚሹ የሰውነት ክፍላችን ውስጥ አንዱ አይናችን ነው።

  በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ የአይን ህክምና ባለሙያ የሆኑት ዶክተር ኪምበርሊይ ኮኬርሃም፥ አሁን አሁን በርካታ ወጣቶች ላይ የአይን ጤና ችግር በብዛት እየተስተዋለ መጥቷል ይላሉ። ይህ ሊሆን የቻለውም በእለት ተእለት እንቅሰቃሴያችን ውስጥ የተለያዩ ስራዎችን ስንሰራ ለአይናችን ተገቢውን ጥንቃቄ ስለማናደርግለት ነው ሲሉም ይናገራሉ።

  አሁን ላይ በብዛት ለአይን ህመም መንስዔ እየሆኑ ከሚገኙ ነገሮች ውስጥ የስክሪን አጠቃቀማችን ማለትን እንደ ላፕቶፕ፣ ስማርት ስልክ፣ ቴሌቭዥን እና ታብሌት ስክሪን በዋናነት ይጠቀሳል።

  ከዚህ በተጨማሪም ከፍተኛ የሆነ ጭንቀት፣ ጤናማ ያልሆነ የአመጋገብ ስርዓት፣ ሲጋራ ማጨስ እና ከመጠን ያለፈ የሰውነት ክብደትም ለአይን ህመም መንስኤ መሆናቸውን ዶክተር ኪምበርሊይ ይናገራሉ።

  አይናችንን የሚጎዱ እና ለመከላከል ማድረግ ያለብን ተግባራት…

  1. የስክሪን አጠቃቀማችን

  ከኤሌክትሮኒክስ ቁሶች ስክሪን የሚወጣው ሰማያዊ ብርሃን የአይናችን እይታ ላይ ጉዳት ከሚያደርሱት ውስጥ አንዱ ነው። ከዚህ በተጨማሪም ረጅም ሰዓት እንደ እንደ ላፕቶፕ፣ ስማርት ስልክ፣ ቴሌቪዥን እና ታብሌት ስክሪኖች ላይ በምናሳልፍበት ጊዜ አይናችን በመሃል እየጨፈንን እረፍት የማንሰጠው ከሆነ ለአይን መድረቅ፣ ለአይን ህመም እና የአይናችን እይታ እንዲደክም ያደርጋል።

  vision-eyesight-eyes-sore-tired-strain-screensየስክሪን አጠቃቀማችን

  በስክሪን ምክንያት እንዲህ አይነት ችግሮች እንይከሰትብን በአይናችን እና በስክሪን መካከል ያለው ርቀት ቢያንስ 16 ኢንች መሆን አለበት የተባለ ሲሆን፥ ከዚህ በተጨማሪም በስክሪኑ ላይ የምናየውን የፅሁፍ መጠን ማሳደግ ለአይናችን ጤንነት ይረዳል።

  READ  ጤናማ እንቅልፍን ለመተኛት የእንቅልፍ ሳይንቲስቱ ሶስት ነገሮችን ይመክራሉ

  2. ጭንቀት

  ሰዎች በሚጨነቁበት ጊዜ የሚያመነጩት ኮርቲሶል የተባለ ሆርሞን በአይን ላይ እክል ይፈጥራል ተብሏል።በጭንቀት ወቅት የሚመነጨው ሆርሞንም እይታችን እንዲደበዝዝ ማድረግ እንደሚችልም ነው ባለሙያዎች የሚናገሩት። በጭንቀት አማካኝነት የሚከሰተውን የእይታ እክል ለመከላከልም ጭንቀትን የሚያስወግዱ እንደ አካል ብቃት እንቅስቃሴ ያሉ ተግባራትን መከወን መልካም ነው፤ በዚህም የኮርቲሶል መጠንን በ25 በመቶ በመቀነስ በአይናችን ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት መቀነስ ይቻላል።

  3. የምናነበውን ነገር ለአይናችን በጣም ማቅረብ

  ከመፅሃፍትም ይሁን ከስልካችን ላይ የምናነባቸውን ነገሮች ወደ አይናችን በጣም የምናቀርብ ከሆነ ይህም በይናችን ጤንነት ላይ እክል ይፈጥራል የሚለውም ተቀምጧል። በዚህ መልኩ የሚከሰት የአይን ጤና እክልን ለመከላከልም በምናነብበት ጊዜ 20-20-20 ህግን መተግበር መልካም ነው።ይህም በምናነብበት ጊዜ በ20 ደቂቃ ልዩነት ለአይናችን እረፍት መስጠት ሲሆን፥ በዚህ ጊዜም ራቅ ወዳሉ እና ለየት ያሉ ነገሮችን መመልከት መልካም ነው።

  4. ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ በአይን ላይ የሚያመጣው እከል

  በአመጋገባችን ውስጥ አትክልት እና ፍራፍሬን የማናካትት ከሆነ ለአይናችን ጠቃመኒ የሆኑ እንደ ኒትሬትስ እና ሉተዪን ያሉ ንጥረ ነገሮችን እንዳናገኝ ያደርጋል። በዚህ መልኩ በአይናችን ላይ የሚደርሱ የጤና እክሎችን ለመከላከልም አትልክቶችን አዘውትሮ መመገብ መልካም ነው፤ በእለት ምግባቸው ውስጥ 240 ሚሊግራም አትክልት አካተው የሚመገቡ ሰዎች ለግላኮማ የመጋለጥ እድላቸውን በ30 በመቶ እንዲቀንሱ ያስችላቸዋል።

  www.menshealth.com

  Read more »

 • ስለ ደም ዓይነቶች ምን ያህል ያውቃሉ?/ ABO blood Group System

   

  (በዳንኤል አማረ ©ኢትዮጤና)

  የደም ዓይነት በቀይ የደም ሴሎች ሽፋን(ገጽ) ላይ የሚገኝ በውርስ የወሰድነውን አንቲጅን(Antigen) መሠረት ያደረገ የደም ክፍፍል ነው፡፡ አራት ዋና ዋና የደም ዓይነቶች አሉ እነሱም ኤ፣ ቢ፣ ኤቢ እና ኦ ናቸው፡፡ የደም ዓይነት ከእናትና አባት በወረስነው ዘረመል(ጂን) ይወሰናል፡፡ ሰውነታችን በአማካይ ከአራት እስከ ስድስት ሊትር ደም ይይዛል፡፡ ደም ከቀይ የደም ሴል፣ ነጭ የደም ሴል እና ፕሌትሌትስ (በፈሳሽ መሰል ፕላዝማ) የተሰራ ወይም የተገነባ ነው፡፡ የፕላዝማ(Plasma) 90% ውሃ ሲሆን በተጨማሪ ፕሮቲን፣ ሆርሞንና ውጋጅ ቆሻሻዎችን ይዟል፡፡ የደማችን 60% የሚሆነው ፕላዝማ ሲሆን 40% የሚሆነው ደግሞ የደም ሴሎች ናቸው፡፡ የደም ሴሎቻችን እያንዳንዳቸው የራሳቸው ተግባር አላቸው ቀይ የደም ሴሎች ኦክስጂን ወደተለያየ የሰውነት ክፍል ያደርሳሉ ካርበን ዳይኦክሳይድ እና ቆሻሻዎችን ከሰውነታችን ያስወግዳሉ፤ ደም ቀይ ቀለም እንዲኖረው አድርገውታል፡፡ ነጭ የደም ሴሎች ሰውነታችን በሽታ የመከላከል ሥርዓት አንዱ ክፍል ሲሆን ኢንፌክሽንን በመዋጋት ይረዳናል፡፡ ፕሌትሌትስ ደም እንዲረጋ በማድረግ የደም መፍሰስን ይከላከላሉ፡፡

  EthioTena's photo.

  የደም ዓይነታችን የሚለየው/የሚታወቀው በደም ውስጥ በሚገኙ አንቲጅን(Antigen) እና አንቲበዲ(Antibody) አማካይነት ነው፡፡ አንቲበዲ(Antibody) ሰውነታችን ከውጪ ለሚገቡ ጀርሞችን ለመከላከል የሚጠቀምበት የበሽታ መከላከያ ሥርዓት ክፍል ነው፡፡ አንቲጅን በቀይ የደም ሴሎች ገጽ ላይ የሚገኙ ፕሮቲኖች ናቸው አንቲበዲዎች በፕላዝማ ውስጥ የሚገኝ ፕሮቲን ሲሆን ከውጭ ወደሰውነታችን የገቡ ማንኛውንም ነገሮች በመለየት እንዲወገዱ ለበሽታ የመከላከል ስርዓት ጥቆማ ያደርጋል፡፡

  የኤ.ቢ.ኦ የደም ሥርዓት ክፍፍል ምን ይመስላል?

  አራት ዋና ዋና የደም ዓይነቶች አሉ፡፡
  • ኤ(A)፦ በቀይ የደም ሴል ላይ ኤ አንቲጅን ብቻ ይገኛል (በፕላዝማ ውስጥ ደግሞ ቢ አንቲበዲ ይገኛል)፡፡
  • ቢ(B)፦ በቀይ የደም ሴል ላይ ቢ አንቲጅን ብቻ ይገኛል (በፕላዝማ ውስጥ ደግሞ ኤ አንቲበዲ ይገኛል)፡፡
  • ኤቢ(AB)፦ በቀይ የደም ሴል ላይ ኤ እና ቢ አንቲጅን ይገኛሉ (በፕላዝማ ውስጥ ደግሞ ምንም ዓይነት አንቲበዲ አይገኝም)::
  • ኦ(O)፦ በቀይ የደም ሴል ላይ ምንም ዓይነት አንቲጅን አይገኝም (በፕላዝማ ውስጥ ሁለቱም ኤ እና ቢ አንቲበዲ ይገኛሉ)፡፡

  የትኛው የደም ዓይነት ለየትኛው የደም ዓይነት መስጠት ይችላል?
  ✓ ኦ(O) የደም ዓይነት ለማንኛውም ሰው ደም መለገስ ይችላል፡፡
  ✓ ኤ(A) የደም ዓይነት ያለው ሰው ኤ እና ኤቢ የደም ዓይነት ላለቸው ደም መለገስ ይችላል፡፡
  ✓ ቢ(B) የደም ዓይነት ያለው ሰው ቢ እና ኤቢ የደም ዓይነት ላለቸው ደም መለገስ ይችላል፡፡
  ✓ ኤቢ(AB) የደም ዓይነት ያለው ሰው ኤቢ የደም ዓይነት ላለው ሰው ብቻ ደም መለገስ ይችላል፡፡

  ከየትኛው የደም ዓይነት መቀበል ይችላሉ?
  ✓ ኦ(O) የደም ዓይነት ካለዎት ከ ኦ(O) ብቻ ይቀበላሉ፡፡
  ✓ ኤ(A) የደም ዓይነት ካለዎት ከ ኤ(A) እና ከ ኦ(O) ብቻ ይቀበላሉ፡፡
  ✓ ቢ(B) የደም ዓይነት ካለዎት ከ ቢ(B) እና ከ ኦ(O) ብቻ ይቀበላሉ፡፡
  ✓ ኤቢ(AB) የደም ዓይነት ከማንኛውም የደም ዓይነት መቀበል ይችላሉ፡፡

  ከኤ(A) እና ቢ(B) አንቲጅን በተጨማሪ ሌላ ሶስተኛ አንቲጅን አለ እሱም አር.ኤች ፋክተር(Rh factor) ይባላል፡፡ በደም ውስጥ ሊኖርም ላይኖርም ይችላል በደም ውስጥ ሲገኝ ፖዘቲቭ (+) ይባላል በደም ውስጥ ሳይገኝ ሲቀር ደግሞ ነጌቲቭ(_) ይባላል፡፡
  በአጠቃላይ አር.ኤች ነጌቲቭ ደም አር.ኤች ነጌቲቭ እና አር.ኤች ፖዘቲቭ ደም ላላአቸው ሰዎች ይሰጣል ወይም አር.ኤች ነጌቲቭ ደም አር.ኤች ፖዘቲቭ ለሆኑ ሰዎች ሊሰጥ ይችላል፡፡

  መልካም ጤንነት!!

  ለበለጠ የጤና መረጃ ይህን ገጽ ላይክ ያድርጉ www.facebook.com/EthioTena

   
  Read more »

 • አያት የልጅ ልጃቸውን ወለዱ

  አያት የልጅ ልጃቸውን ወለዱ

   

  አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሜሪካ ሰሜናዊ ቴክሳስ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ የልጅ ልጃቸውን ወልደዋል።

  ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል…? የሚል ጥያቄ ማስከተሉ አይቀርም።

  ነገሩ እንዲህ ነው የ54 ዓመቷ ትሬሲ ቶምሰን የ28 ዓመት ልጃቸው በማህፀኗ አርግዛ መውለድ እንደማትችል ይነገራቸዋል።

  በዚህ ጊዜም ልጃቸው ከዶክተሮቹ የቀረበላት አማራጭ በሌላ ሰው ማህጸን ውስጥ የሷ እና የባሏ ዘር ተወስዶ እንዲረገዝ ማድረግ ነበር።

  ታዲያ ይህንን የሰሙት ትሬሲ የልጃቸው እና የልጃቸው ባል ዘር በማህፀናቸው ውስጥ እንዲያድግ ፈቃደኛ ይሆናሉ።

  እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ባሳለፍነው 2015 ሚያዝያ ወር ዘሩ በአዛውንቷ ማህፀን ውስጥ ገብቶ ፅንሱ በማህጸናቸው ውስጥ እንዲያድግ መደረጉን ዶክተሮች ይናገራሉ።

  አያትም የልጅ ልጃቸውን በማህጸናቸው ለዘጠኝ ወራት ይዘው ቆይተው በሰላም መገላገላቸውን ዶክተሮቹ ባሳለፍነው ሳምንት ሀሙስ አስታውቀዋል።

  የልጅ ልጅ የመሳም አምሮታቸውንም አያት ወልደው ህልማቸውን ማሳካት መቻላቸውን ዘገባው አትቷል።

  ህጻኑ ልጅ ክሌሲይ የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን፥ ይህም ከእናቱ እና ከአያቱ የተወጣጣ ነው ተብሏል።

  በአሁኑ ጊዜ አያት እና ልጅ በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ።

   

  ምንጭ፦ www.emirates247.com

   

  Read more »

 • የሚግሬን ራስ ህመም ምንድን ነው? what is a Migraine headache?

  የሚግሬን ራስ ህመም ምንድን ነው (What is a Migraine headache)
  (በዳንኤል አማረ ©ኢትዮጤና)

  ሚግሬን የራስ ህመም በአእምሮ ውስጥ የሚፈጠሩ ለውጦች ውጤት ነው፡፡ ከፍተኛ የራስ ህመም ያስከትላል ይህን ተከትሎ በብርሀን መብራት ፣ድምጽና ሽታ በሽተኞቹ በቀላሉ ይረበሻሉ፡፡
  የሚግሬን ህመም የሚከሰተው ጭንቅላታችንን ለሁለት በመክፈል በአንድ ክፍል/አቅጣጫ ብቻ ነው፡፡ በአንዳንድ በሽተኞች ላይ በሽታው ከመከሰቱ በፊት የተለየ የማስጠንቀቂያ ምልክት ማየት ይጀምራሉ ይህም ምልክት የብርሀን ነጸብራቅ ወይም ጥቁር ነጭ በአንድ አይናቸው ላይ ከማየት ጀምሮ እስከ ድካም (ግማሽ የሰውነት ክፍል) ሊደርስ ይችላል ፡፡ ይህ ምልክት ለጥቂት ደቂቃዎች ይቆዩና የራስ ህመሙ ሲጀምር ምልክቱ ማየት ያቆማሉ፡፡
  ሁሉም የራስ ምታቶች ሚግሬንን አይወክሉም በተጨማሪም ሚግሬን ብቸኛው ከፍተኛ የራስ ህመም የሚያስከትል እንዳልሆነ ልብ ልንል ይገባል፡፡

  ✔የሚግሬን በሽታ እንዴት ይነሳል
  በብዙ ምክንያቶች የሚግሬን በሽታ ይቀሰቀሳል፡፡ ከነዚህም መካከል 
  • የሆርሞኖች መለዋጥ በተለይ በወር አበባ ጊዜ ሴቶች ለሚግሬን ራስ ምታት እንዲጋለጡ ያደርጋል 
  • አንዳንድ የወሊድ መቆጣጠርያዎች ሚግሬንን ይቀሰቅሳሉ 
  • የተለያዩ ምግቦች ለምሳሌ 
  o ቀይ ወይን 
  o የቆዬ አይብ
  o ስጋ ሳይበላሽ እንዲቆይ የሚያደርጉ ጭሶች (ሬት ናይት)
  o ሞኖሶዲየምግሉታሜት
  o ሰው ሰራሽ ማጣፈጫዎች
  o ቸኮሌት
  o የእንስሳት ተዋጽኦዎች
  o ከመጠን በላይ መተኛት
  o የአልኮል መጠጦች
  o ጭንቀት
  o ለከፍተኛ ቀስቃሽ ነገሮች መጋለጥ እንደ ከፍተኛ ብርሀን ከፍተኛ የሚጮህ ድምጽ እና ከባድ ሽታዎች ናቸው

  ✔የሚግሬን በሽታ መነሻ ምንድን ነው
  ትክክለኛው የሚግሬን በሽታ በመነሻው ባይታወቅም በአእምሮ ሴሎች መካከል መልእክት የሚያስተላልፍ ኬሚካሎች መለዋወጥ ለዚህ በሽታ መነሻ ይሆናል ተብሎ ይገመታል፡፡
  ለሚግሬን በሽታ የሚያጋልጡ ነገሮች ምንድን ናቸው 
  • በሚግሪን ከተያዙ 25 ፐርሰንት የሚሆኑ በሂዎታቸው በሆነ አጋጣሚ ለዚህ በሽታ ይጋለጣሉ፡፡
  • አብዛሀኛዎቹ የሚግሪን ተጠቂዎች ሴቶች ናቸው ከጉርምስናና ወጣትነት ግዜ በኋላ በበሽታው የመጠቃት ንጥጥር ሴት ለወንድ 3 ለ 1 ነው፡፡ የቤተሰብ የዘር ሀረግ በሚግሬን በሽታ የሚጠቁ ከሆነ እርሰዎም የመያዝ እድል አለዎት ፡፡

  ✔የሚግሬን በሽታ ምልክቶች
  መደበኛ /የተለመዱ የሚግሬን በሽታ ምልክቶች እነሆ 
  • በግማሽ የጭንቅላታችን ክፍል ከባድ የራስ ህመም
  • ማቅለሽለሽና ማስታወክ
  • በብርሀን/መብራት በቀላል መረበሽ
  • በከፍተኛ ጩኸት/ድምጽ በቀላል መረበሽ 
  • የአይን ህመም ናቸዉ
  የሚግሪን በሽታ ክፍል/ደረጃ ያለው ህመም፤የትርታ መረበሽ፤መረበሽ በአካላዊ እንቅስቃሴዎች/ተግባሮች የሚነሳ እና ከማቅሽለሽና ትዉከት የተያያዘ በተጨማርም ፎቶፎቢያ እና ፎኖፎቢያ (ለብርሀንና ድምጽ ጥላቻ መኖር ) በሽታ በማለት አለም አቀፍ የራስ ህመም ማህበር ይገልጸዋል ፡፡
  የሚግሪን በሽታ ህመም ከጀመርን ከጥቂት ሰአት/ቀናቶች ይችላል፡፡በችኮላ መራመድ/መሄድና ወደ ከፍታ ቦታዎች ለምሳሌ ፎቅ ስንወጣ የበሽታዉን ህመም ያባብስዋል፡፡አንድ ሶስተኛ የሚሆኑት በሽተኞች የተለየ ምልክቶች ይኖራቸዋል፡፡ይህ ምልክት ጊዜያዊ የእይታ መስተጓጎል ሲሆን በምናየው ነገር ላይ ክብ ጥቁር ነጥብ መታየት እና አንፀባራቂ ብርሃን በአንድ ወይም ሁለት አይናችን ዉስጥ ማየት ነው፡፡አልፎ አልፎ ግማሽ የሰዉነታቸን ክፍል መዛል/መድከም ሊከሰት ይችላል፡፡ የተለየ አካላዊ ምልክቶች በሚግራን በሽታ ላይ አይታይባቸዉም፡፡

  ✔ የሚግሬን በሽታ ህክምና
  አለም አቀፍ የራስ ህመም ድርጅት እንዳወታዉ ክፍፍል ከሆነ አንድ ሰዉ የሚግራን በሽተኛ ለመባል ቢያንስ 5 ጊዜ የራስ ህመም ሲያጋጥመዉ እና የሚከተሉትን መመዘኛዎች ሲያማላ ነዉ፡፡
  • ከ4-72 ሰአት የሚቆይ የራስ ህመም 
  • የራስ ህመሙ ከሚከተሉት ሁለት ምልክቶች ለኖሩት ግድ ይላል ፡ወትነት ያለዉ ወይም ተመሳሳይ ቦታ ላይ፤ የልብ ምት በጭንቅላት አካባቢ 
  • መካከለኛ ወይም ከባድ የህመም ደረጃ 
  • የሚከተሉትን አካላዊና ስናደርግ የሚባባስ ወይም ለመተግበር አለመፈለግ ለምሳሌ ስንራመድ ስንሄድ ወይም ደረጃ /ፎው ስንወጣ የሚባባስ ከሆነ 
  • በራሽ ኅመም ጊዜ አንድ ሲኖር 
  • ማቅለሽለሽ ወይም ማስታወክ 
  • ፎቶ ፎቢያና/ወየም ፎኖፎቢያ
  • የራስህመምሙ ወደ ሌላ ችግሮች /ህመሞች የማይሸጋገር ከሆነ ናቸው ፡፡

  ✔የሚግሬን በሽታ መድሀኒቶች 
  የሚግሬን በሽታ መድሀኒቶች የሚወሰነው የራስ ህመሙ በምንያህል ድግግሞሽ ይከሰታል
  እና ይህ ህመም ለምን ያህል ግዜ ይቆያል በሚል ሀሳቦች ላይ ነው 
  የሚግሬ እራስ ህመም የተለያየ ሲሆን እንደ አሲታሚ ሆፊን ወይም አቡፕሮፊን እንዲሁም የመድሀኒቶችን ያጠቃልላል፡፡ 
  • ትሪኘቴንስ
  • ትሬኘቴንስ(ሱማትሪኘቴን፣ሪዘትሪንቴን፣ኢሊትሪፕቴን፣ዞልሚትሪፕቴን፣ናራትረፕቴን አልሞትቴን እና ፈሮቫትረፕቴን ሲሆኑ የሚግሬን ህምም በከፍተኛ ሁኔታ የማዳን ብቃት አላቸው፡፡
  • ማንኛውም የሚግሬን በሽተኞች እነዚህን መድሀኒቶች መውሰድ የለባቸውም እነዚህ መድሀኒቶች ለመውሰድ የተለያየ እገዳ የሚደረግባቸው በሽተኞች ይኖራሉ፡፡
  • አንዳንድ መድሀኒቶች በቤት ውስጥ ሊወሰድ የሚችሉ ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ በጠየና ባለሙያዎች እያለ ውስጥ ሆነው የሚወሰድ ናቸው፡፡
  • ናርኮቲን የናርኮቲክስ መድሀኒቶች የሚግሬን በሽታን ለማከም ተመራጭ አይደለም እነዚህ መድሀኒቶች የራስ ህማችን ድጋሜ በሚያምን ጊዜ የምንጠቀማቸው ናቸው፡፡

  ✔ራሳችንን የማከምና የአኗኗር ለውጦች 
  በሚግሬን በሽታ የሚሰቃዩ ሰዎች የህሙማን ድግግሞሽ ና ጥንካሬ ለመቀነስ ከፍተኛ ሚና መጫዎት ያለብን ስራሳችን ነን፡፡ ለራስ ህመም የሚያጋልጡንን ምክንያቶች ጠንቅቀን ካላየናቸው በኋላ የአኗኗር ዘይቤን ማሻሻል ህመሙን ይቀንሰዋል፡፡ የሚከተሉትን ተግባራዊ ያድርጉ፤፤
  • የምንመገብበትና የምንተኛበት ሰአታችንን መደበኛ ፕሮግራም ማድረግ( ሁል ጊዜ በተመሳሳይ ሰዓት) 
  • በሽታን ሊቀንሱ የሚችሉ ምግቦችን መመገብ ማቆም
  • የፈሳሽ ድርቀትን ማስወገድ ምክንያም እጥረት እንዳንድ ሰዎችን በሽታውን ሊቀንስባቸው የሚችል ነው 
  • መደበኛ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች

  ✔እንቅስቃሴ እና ሚግሪን
  አንዳንድ ሰዎች ጡንቻዎችን የሚያፍታቱ ስፖርቶች ሲሰሩ የሚግሬን ህመምን ይቀንስላቸዋል፡፡ ለዚህ ምሳሌ የሚሆኑ የአአምሮና ሰውነት ውህደቶች የሚጠይቁ ስፖርቶች መካከል 
  • ሜዲቴንሽን(መመሰጥ)
  • የጡንቻዎች ማፍታቻ ስፖርቶች
  • ዮጋ
  • በግጥም ሙዚቃና ስእሎች መመሰጥ

  ✔አመጋገብና ሚግሬን
  ለሚግሪን በሽተኞች የሚሆኑ የተለያዩ ምግቦች የሉም ነገር በላይ እንደተጠቀሰዉ የሚግሬንን ህመም የሚቀሰቅሱ ምግች ከመዉሰድ መቆጠብ ነዉ፡፡
  የአልኮል መጠጦች የአንዳንዱ ሰዎችን ሚግሬን በሽታን ይቀሰቅሳሉ፡፡

  መልካም ጤንንት!!!
  ለበለጠ የጤና መረጃ ይህን ገጽ ላይክ ያድርጉት
  www.facebook.com/EthioTena

  Read more »